ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በጥር 07 ቀን 2011 ዓ.ም. በናይሮቢ ኬኒያ በዱሲት ዲ2 ሆቴል ላይ በአልሸባብ ሽብርተኞች የደረሰውን ጥቃት በማቀድ እገዛ ስላደረገው የአል-ሸባብ አመራር አባል መሐሙድ አብዲ አደን መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ወሮታ ይከፍላል፡፡ በዚህ ጥቃት ፈንጂዎች፣ አውቶማቲክ መሣሪያ እና ቦምቦች የያዙ የአልሸባብ ታጣቂዎች መደብሮች፣ ቢሮዎች እና ሆቴል በያዘው ባለ ስድስት ፎቅ ዱሲት ዲ2 የንግድ ማዕከል ላይ ጥቃት ፈጸሙ፡፡ በዚህ ጥቃት የዩናትድ ስቴትስ ዜጎችን ጨምሮ ቢያንስ 21 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በጥቅምት 2015 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይማንን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ (SDGT) በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡
