ማሊም አይመን

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትህ በኬኒያ እና ሶማሊያ የሽብር ጥቃት የፈጸመው የአልሸባብ ዩኒት ጃይሽ አይማን መሪ ስለሆነው ማሊም አይማን መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በታኅሳስ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. የአል-ሸባብ ሽብርተኞች በማንዳ ቤይ የአውሮፕላን መስክ ላይ በነበሩ የኬኒያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ላይ ጥቃት ፈጸሙ፤ በዚህ ጥቃት ሁለት የአሜሪካ የኮንትራት ፓይለቶች እና አንድ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪነት በመሥራት ላይ የነበረ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል ስፔሻሊስት ተገድለዋል፡፡ ሦስተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ኮንትራክተር እና ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የሰርቪስ አባላት በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ማሊም አይማን በጥር 2012 ዓ.ም. ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነት ይወስዳል፡፡ በኅዳር 2013 ዓ.ም.፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይማንን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ (SDGT) በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (EO) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡

ማንዳ ቤይ ፋሲሊቲ የኬኒያ የመከላከያ ኃይል የጦር ሰፈር ሲሆን፣ ዩናይትድ ሰቴትስ የምሥራቅ አፍሪካ አጋሮቿ ለሽብር ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ እና በክልሉ የአሜሪካን ጥቅሞች ለማስጠበቅ ሥልጠና ለመስጠት እና ለጸረ- ሽበር ድጋፍ የምትጠቀምበት ስፍራ ነው፡፡

Skip to content