ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ሐማስ ተብሎ የሚታወቀውን ሽብርተኛ ድርጅት ወይም በሌላ ስሙ ሃረካት አል-ሙቃዋማ አል-ኢስላሚያ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
መሐመድ አሕመድ አብድ አል-ዳዪም ናስረላህ በኳታር ውስጥ የሚሰራ የረጅም ጊዜ የሐማስ አባል ሲሆን፣ ከኢራን ድርጅቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት አለው፡፡ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለሐማስ በማስተላለፍ ላይ ተሳትፎ የነበረው ሲሆን፣ ካስተላለፈላቸውም አካላት መካከል የሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ኢዝ-ዲን አል-ቃሲም ብርጌድይገኝበታል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት 07 ቀን 2016 ዓ.ም. ናስረላን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ 13224 መሠረት ሰይሞታል፡፡ በዚህ መልኩ መሰየሙም የሽብር ጥቃት በሚፈጽሙ ወይም ከፍተኛ የመፈጸም ዕድል ያላቸውን የውጭ አገር ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች ላይ ዕግድ ይጥላል፡፡ ከዚህም ሌላ ይህ ትዕዛዝ የዩይነትድ ስቴትስ መንግሥት በዚህ ትዕዛዝ ስር ሽብርተኞች እና የሽብር ድርጅቶች ተብለው ለተሰየሙት ወይም ለእነርሱ የበታች ድርጅቶች፣ ሽፋን ሰጪዎች፣ ወኪሎች ወይም ተባባሪዎች ድጋፍ፣ አገልግሎቶች ወይም እገዛ የሚሰጡትን ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች እንዲያግድ የሚያዝ ነው፡፡
