ሙሃመድ አብዱላህ ኸሊል ሁሴን አር-ራሃያል

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሙሃመድ አብዱላህ ኸሊል ሁሴን አር-ራሃያል፣ በሌላ ስሙ ኸሊል አንትዋን ኢዋን እና ኸሊል አሊድ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አር-ራሃያል አል-ሙናዋር አቡ ኒዳል የተባለው የሽብርተኞች ድርጅት አባል ነው ይባላል፤ እርሱም በካራቺ በነሐሴ 30 ቀን 1978 ዓ.ም. በፓን አም በረራ 73 በተፈጸመው የአውሮፕላን ጠለፋ ላይ ለነበረው ተሳትፎ ይፈለጋል፡፡ 379 ተሳፋሪዎችን እና የበረራ ሠራተኞችን ለ16 ሰዓታት ያህል አግተው ካቆዩ በኋላ፣ አጋቾቹ በጭፍን ተኩስ ከፈቱ፤ በዚህም ሁለት አሜሪካዊያንን ጨምሮ ሃያ ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡

አር-ራሃያል በዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ግራንድ ጁሪ የቀረበበትን ክስ ይከላከል የሚል ውሳኔ የተላለፈበት ሲሆን፣ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡ አር-ራሃያል በመካከለኛው ምሥራቅ ነዋሪ ነው፡፡

Skip to content