ሆሴይን ሃቴፊ አርዳካኒ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 15 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በዩናይትድ ስቴትስ ሽብርተኛ ተብሎ የተሰየመውን የኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ጓዶች የፋይናንስ (ኢስላሚክ ሪቮሉሽነሪ ጋርድ ኮርፕስ) ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

ሆሴይን ሃቴፊ አርዳካኒ ኢራናዊ ዜግነት ያለው ነጋዴ ነው፤ እርሱም ለኢስላሚክ ሪቮሉሽነሪ ጋርድ ኮርፕስ የመሣሪያ ምርት እና ሽያጭ እገዛ ያደርጉ ውስብስብ ቴክኖሎጂ እንዲገኝ እና እንዲቀርብለት እገዛ አድርጓል፡፡ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ አርዳካኒ በማሌዢያ እና በበሆንግ ኮንግ የተሰማሩ እና ሌሎችንም ልዩ ልዩ መካከለኛ ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች በመጠቀም እጅግ ወሳኝ የሆኑ በዩናይትድ ስቴትስ እና በውጭ አገራት የሚሰሩ ምርቶችን፣ የእነርሱን ክፍሎች እና ቴክኖሎጂዎች ለኢራን ኢስላማዊ ሪፑብሊክ (ኢራን) የጦር መሣሪያዎች ፕሮግራሞች እንዲውሉ አድርጓል፡፡ እነዚህ የጦር መሣሪያዎች ለምሳሌ ሻህድ-136 እና ሻህድ-131 የተባሉ ሰው አልባ ጥቃት ፈጻሚ አውሮፕላኖች (ዩኤቪ ወይም ድሮኖች) ስለ ኢስላሚክ ሪቮሉሽነሪ ጋርድ ኮርፕስ ተመርተው በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተሽጠዋል፡፡ እንዲህ ካሉት ድሮኖች መካከል ለሩሲያ የጦር ኃይል ተሽጠው በዩክሬን በሚካሄደው ሕገወጥ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች ላይ ውለዋል፡፡

የአርዳካኒ ኔትወርክ በዩክሬን እና በሌሎች ግጭት ባለባቸው አገራት በወደቁ የሻሄድ ድሮን ስብርባሪዎች ውስጥ ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም የአርዳካኒ ኔትወርክ በዩናይትድ ስቴትስ የኤክስፖርት ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ከፍተኛ የኤሌክትሮን እንቅስቃሴ ያላቸውን ትራንዚስተሮች (በሌላ መጠሪያቸው ሄኢኤምቲ ተብለው የሚታወቁ) እና ሌሎች ለባለስቲክ ሚሳኤል የሚያገለግሉ ክፍሎች እንዲሁም ሌሎች ለመሣሪያ ምርት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በሕገወጥ መንገድ ገዝቷል፡፡

በማሌዢያ የሚሰሩ እና ለአርዳካኒ ኔትወርክ እገዛ ከሚያደርጉ ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች መካከል አርታ ዌቭ ኤስዲኤን ቢኤችዲ፣ ኢንተግሬትድ ሳይንቲፊክ ማይክሮዌቭ ቴክኖሎጂስ እና ቴክኖሎጂ መራክ ኤስዲኤን ቢኤችዲ ይገኙባቸዋል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች እና እነዚህ እና ሌሎች ኩባንያዎች በኳላ ላምፑር፣ ማሌዢያ በድርጅትነት ተመዝግበዋል፤ በሆንግ ኮንግ ደግሞ ያልተመዘገበ ወኪል እና የጋራ አድራሻዎች አሏቸው፡፡ ኩባንያዎቹ የአርዳካኒ ወኪሎች በመሆን የዩናትድ ስቴትስ እና በሌሎች አገራት የተመረቱ ማቴሪያሎች እንዲያገኝ ያግዙታል፤ ይህ ባይሆን ኖሮ ግን በዩናይትድ ስቴትስ በኢራን እና በኢስላሚክ ሪቮሉሽነሪ ጋርድ ላይ በተጣሉ ማዕቀቦች እና በኤክስፖርት ቁጥጥር ምክንያት አርዳካኒ ማቴሪያሎቹን በሕጋዊ ግዢ ሊያገኛቸው አይችልም ነበር፡፡

በዱባይ የሚገኙት ስማርት ሜይል ሰርቪስስ፣ ሪንግ ፊልድ ኤፍዜድኢ እና ሌሎች በማጭበርበር የጭነት ሁኔዎችን የሚያመቻቹ እና የሃሰት የጭነት መረጃዎች በማቅረብ ዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎችም የተጣሉትን ማዕቀቦች እና የኤክስፖርት ቁጥጥር ደንቦች በማለፍ በሕገወጥ መንገድ የተገዙ ዕቃዎችን ስለ አርዳካኒ ለኢስላሚክ ሪቮሉሽነሪ ጋርድ ኮርፕስ ያቀርባሉ፡፡

እንዲሁም አርዳካኒ በቴህራን የሚገኙ ካቫን ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ ሊሚትድ፣ ባሳማድ ኤሌክትሮኒክ ፑኦያ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ እና ተይፍ ታድቢር አርያ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ የተባሉ ድርጅቶችን ይመራል፡፡

በታኅሳስ 09 ቀን 2016 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የፍትሕ ሚኒስቴር በአርዳካኒ ክስ መስርቷል፤ በክሱም አርዳካኒ በዩናይትድ ስቴትስ የተመረተ ለድርብ ዓላማ ሊውል የሚችል ማይክሮኤሌክትሮኒክስ ለኢስላሚክ ሪቮሉሽነሪ ጋርድ ኮርፕስ ሽጧል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ ገንዘብ ሚኒስቴር በሥራ አስፈጻሚ (ኤግዘኪውቲቭ ኦርደር) 13382 መሠረት በልዩ ትኩረት የተመዘገቡ ዜጎች በሚል ዝርዝር ውስጥ አርዳካኒን እና 10 ሌሎች ተቋማትን አካትቷል፤ ይህ ትዕዛዝ ጅምላ ጨራሽ መሣሪያዎችን እና የእነርሱን ማስረከቢያ ዘዴዎች ዒላማ ያደረገ ነው፡፡ ማዕቀቦቹ የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ምንም ዓይነት ልውውጥ እንዳያደርጉ ወይም በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እገዳ የተጣለባቸው ወይም በሽብርተኝነት የተሰየሙ ሰዎች ንብረቶችን የሚያካትቱ ማናቸውም ልውውጦች እንዳይካሄዱ (ዩናይትድ ስቴትስን በማለፍ የሚደረጉ ልውውጦችን ጨምሮ) ክልከላ ያደርጋል፡፡

Skip to content