ሃሰን ኢዝ-አል-ዲን

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሀሰን ኢዝ- አል- ዲን በሌላ ስሙ አህመድ ጋርባያ እና ሳሚር ሳልዋን መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ እዝ አል-ዲን የሂዝባላህ አባል በመሆኑ በ1985 በተፈፀመው የቲደብሊውኤ በረራ 847 ጠለፋ በነበረው ሚና ይፈለጋል፡፡

በሰኔ 07 ቀን 1977 ዓ.ም. ሽብርተኞች ከአቴንስ ወደ ሮም በመብረር ላይ የነበረውን ቲደብሊውኤ በረራ 847 ጠልፈዋል፡፡ ለ17 ቀናት ይህ አውሮፕላን 153 ተጓዦች እና የበረራውን ሰራተኞች ይዞ ከቤይሩት ወደ አልጀርስ እና በድጋሚ ወደ ቤይሩት እንዲጓጓዝ ተገዷል፤ በዚህም መልኩ በቤይሩት ለሶስት ጊዜያት አርፏል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤይሩት ሲያርፍ ጠላፊዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ሀይል አሽከርካሪ የነበረውን ሮበርት ስቴተም ክፉኛ ደብድበው በጥይት መትተው ገድለዋል፡፡

በኅዳር 08 ቀን 1978 ዓ.ም.፣ ኢዝ-አል-ዲን በጠለፋ ውስጥ ለነበረው ተሳትፎ እና ሚና በወንጀል እንዲከሰስ ተበይኖበታል፡፡ በጥቅምት 02 ቀን 1994 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢዝ-አል-ዲን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአትዋ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከኢዝ-አል-ዲን ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው የሂዝባላህ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ እንዲሁም አትዋ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፤ በአሁኑ ወቅት በሊባኖስ ይገኛል ተብሎ ይታመናል፡፡

Skip to content