ሃሚድ ኤል ኻይሪ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሀማድ ኤል ኻይሪ በሌላ ስሙ አማዳ ኦዉልድ ኼይሩ ወይም አቦዉ ቁምቁም ሙቭመንት ፎር ዩኒቲ እና ጅሀድ በምዕራፍ አፍሪካ (ኤምዩጄ ደብሊውኤ) የተባለውን ድርጅት በመስራችነት እና በመሪነት ስላለው ሚና መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

በኻይሪ አመራር ስር የሙቭመነት ፎር ዩኒቲ እና ጅሃድ በምዕራብ አፍሪካ አባላት በውጭ አገር ዲፕሎማቶች እና በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሽብር ጥቃት እና የማገት ተግባር ፈፅሟል፡፡ ኻይሪ በሚያዝያ 2004 ዓ.ም. በ7 የአልጄሪያ ዲፕሎማቶች ላይ በማሊ የተፈፀመውን የማገት ተግባር በተመለከተ ሀላፊነት ወስዷል፤ በድርጅቱ ቪዲዮዎች ላይ በመቅረብ ድርጀቱን በሚቃወሙ ማስፈራሪያ አድርጓል፡፡ በጥር 2004 ዓ.ም. ኻይሪ የድርጅቱ ግብ “በመላው ምዕራብ አፍሪካ የሸሪዓ ህግ ተፈፃሚ ማድረግ ነው” ብሏል፡፡

በሙቭመንት ፎር ዩኒቲ እና በጅሀድ በምዕራብ አፍሪካ ድርጅት ውስጥ በአመራርነት ከመቀመጡ በፊት ኻይሪ በእስላማዊ ማግሪብ ውስጥ የአል-ቃዒዳ አባል ነበር፣ በዚያም በሞሪታኒያ ላይ የሽብር ተግባራት አቅዷል፡፡ በጥቅምት 2003 ዓ.ም. ኻይሪ በአልጄሪያ 3 የአውሮፓ የእርዳታ ሰራተኞች እንዲታገቱ ትእዛዝ ሰጠ፤ 2 ደግሞ በጥይት እንዲቆስሉ አድርጓል፡፡

በኅዳር 28 ቀን 2005 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኻይሪ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የኻይሪ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከኻይሪ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡

Skip to content