ሁሳያን ሙሐመድ አል-ኡምሪ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሁሳይን ሜሀመድ አልኡማሪ፣ በሌላ ስሙ ሁሴን መሀመድ አል-ኡማሪ እና አቡ ኢብራሂም መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ኡማሪ በፓን ኤም በረራ ቁ. 1982 ለነበረው ተሳትፎ ይፈለጋል፡፡ አል-ኡማሪ የቦንብ ባለሙያ ሲሆን፣ በአንድ ወቅት 15 ሜይ ድርጅት በመባል የሚታወቀውን የሽብር ቡድን መርቷል፡፡

በነሐሴ 05 ቀን 1974 ዓ.ም. በአል-ኡማሪ ተነድፎ ተሰርቷል ተብሎ የሚገመት ቦንብ 267 ተሳፋሪዎች እና የበረራ ሠራተኞች ይዞ ይጓዝ በነበረ አውሮፕላን ላይ ፈነዳ፤ አውሮፕላኑ ከቶኪዮ፣ ጃፓን ወደ ሆነሉሉ፣ ሃዋይ በመብረር ላይ ነበር፡፡ ይህ ፍንዳታ 16-ዓመት ዕድሜ ያላት አንዲት ተጓዥ ሲገድል በ16 ሌሎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡ አል-ኡምሪ ከቦንብ ፍንዳታው ጋር በያያዘ ከሌሎች ሁለት ተከሳሾች ጋር ክስ ይመስረትበት የሚል ውሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡ እንዲሁም የፈረንሳይ መንግሥት በ1977 ዓ.ም. በማርክስ ኤንድ ስፔንሰር የሸቀጥ መደብር እና በሌዩሚ ባንክ ላይ ለደረሱት የቦንብ ጥቃቶች ክስ ይመስረትበት የሚል ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

አል-ኡምሪ የሊባኖስ ፓስፖርት ያለው ሲሆን፣ በኢራቅ ወይም በሊባኖስ ነዋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ይገኛል፡፡ መከላከያ ሚኒስቴር ይህን ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $200,000 ወሮታ ይከፍላል፡፡

Skip to content