ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ቲደብልዩኤ በረራ 840 የቦምብ ፍንዳታ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በመጋቢት 24 ቀን 1978 ዓ.ም. ከሮም፣ ጣሊያን ወደ አቴንስ፣ ግሪክ በመጓዝ ላይ በነበረው ቲደብልዩኤ በረራ 840 ቦምብ ፈነዳ፡፡ ይህ ፍንዳታ የ9 ወር ሕጻን፣ እናቷን እና አያቷን ጨምሮ አራት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ገድሏል፤ ሁሉም ሟቾች ከአውሮፕላኑ ተስፈንጥረው ወጥተዋል፡፡ አምስት ሌሎች ተጓዦች ደግሞ ተጎድተዋል፡፡ ከቤይሩት በተሰጠ መግለጫ የዓረብ አቢዮታዊ ሕዋሳት (አረብ ሪቮሉሽነሪ ሴልስ) ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስደዋል፡፡

