የፖል ኤድዊን ኦቨርባይ፣ ጁኒየር መታፈን

ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ፖል ኤድዊን ኦቨርባይ፣ ጁኒየር መገኘት፣ ስላለበት አድራሻ እና በደህንነት ስለሚመለስበት ሁኔታ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በግንቦት 2006 ዓ.ም. አሜሪካዊው ጸሐፊ ኦቨርባይ ፣ ጁኒየር በአፍጋኒስታን ኾስት በተባለ ክፍለ አገር ጠፋ፤ በዚያም ለአንድ የመጽሐፍ ፕሮጀክት ጥናት በማካሄድ ላይ ነበር፡፡ ከመጥፋቱ በፊት ኦቨርባይ ምርምሩን ለማካሄድ ወደ ፓኪስታን ድንበር ለመሻገር ዕቅድ እንዳለው ተናግሮ ነበር፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ የታየውም በኾስት ከተማ፣ አፍጋኒስታን ነበር፡፡ ኦቨርባይ ክትትል እና መድኃኒት የሚያስፈልገው የውስጠኛው የጆሮ ካናል ሕመም አለበት፡፡

Skip to content