የኬቨን ስኮት ሱቴ አፈና

ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ

ወሮታ

እስከ 3 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ኬቨን ስኮት ሱታይ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በሰኔ 2005 ዓ.ም. የኮሎምቢያ አቢዮታዊ የጦር ኃይል (ኤፍኤርሲ) የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ሠራዊት አባል የነበረውን ሱታይን አግቶ ወሰደ፤ እገታው የተፈጸመው በኮሎምቢያ በኤል ሬቶርኖ ማዘጋጃቤት አቅራቢያ ነበር፡፡ ሱታይ በበርካታ የደቡብ አሜሪካ ማዕከላዊ እና የደቡብ አገራት በጉብኝት ላይ ነበር፡፡
በሐምሌ 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ኤፍኤአርሲ ስለእገታው ኃላፊነት በመውሰድ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፣ እንደ ቅን ልቦና እርምጃ ማሳያ እንዲሆን ሱታይን ከእገታ ለመልቀቅ ያለውን ሃሳብ አሳወቀ፡፡ ሆኖም ግን ሱቴይ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ሳይለቀቅ ቀረ፤ በዚህም ቀን ለኮሎምቢያ፣ ኩባ እና ኖርዌይ መንግሥታት እና ለዓለም ዓቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ በኋላ ሱቴይ በቦጎታ፣ ኮሎምቢያ ለዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ተሰጥቶ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲበር ተደርጓል፡፡

Skip to content