ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በጥር03 ቀን 1993 ዓ.ም. በአለም የንግድ ማዕከል እና በፔንታገን ላይ ስለተፈፀመው ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $25 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ከአል-ቃዒዳ (ኤኪው) ጋር ግንኙነት ያላቸው 19 ሽብርተኞች ከሶስት የተለያዩ የምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ አየር ማረፊያዎች ተነስተው ወደ ካሊፎርኒያ ይበሩ የነበሩ አራት የንግድ አውሮፕላኖችን ጠለፉ፡፡ ሽብርተኞቹ ሁለት አውሮፕላኖችን በኒውዮርክ ከተማ፣ ኒውዮርክ ከሚገኘው የአለም የንግድ ማዕከል ዋነኛ መንትያ ህንፃዎች ጋር አጋጩ፤ ሶስተኛው ደግሞ በአርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ ከሚገኘው ፔንታገን የምዕራብ ገፅታ ጋር ተጋጨ፡፡ አራተኛው አውሮፕላን ከሻንክስቪር፣ ፔንሲልቫኒያ አካባቢ ተከሰከሰ፡፡ ይህም የሆነው ተሳፋሪዎች አውሮፕላኑን ከጠላፊዎች ለማስጣል ሲሞክሩ ነው፡፡ በጠቅላላው እነዚህ ጥቃት ፈፃሚዎች ከሞላ ጎደል በአለም ዙሪያ የተለያዩ አገራት ዜግነት ያላቸውን 3000 ያህል ዜጎች ገድለዋል፡፡ ሟች የአል-ቃዒዳ መሪ ኡሳማ ቢን ላዲን እነዚህን ጥቃቶች ማቀዱን እና መተግበሩን ከክስተቶቹ በኋላ በለቀቀው የቪዲዮ መልዕክት ሀላፊነት ወስዷል፡፡
ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አውሮፕላኖች ከቦስተን ሎጋን አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የተነሱት አውሮፕላኖች በኒው-ዮርክ ከተማ ከሚገኘው የአለም የንግድ ማዕከል ሁለቱ መንትያ ህንፃዎች ጋር ተጋጭተዋል፡፡ እነዚህ ሁለት አውሮፕላኖች በመጋጨታቸው ከጀት ነዳጅ የተነሳው እሳት የህንፃውን መዋቅሮች በመጉዳቱ ህንፃዎቹ ሊደረመሱ ችለዋል፡፡ በህንፃዎቹ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ከ2,600 በላይ ሰዎች ገድሏል፡፡
ሶስተኛው አውሮፕላን ከዋሽንንግተን ዱለስ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ ሁለተኛው አውሮፕላን ከአለም ንግድ ማዕከል ጋር ከተጋጨ ከአንድ ሰአት በኋላ በፔንታገን የደቡብ ምዕራብ ክንፍ ላይ ወደቀ፡፡ ይህ ክስተት በአውሮፕላኑ የነበሩ ተሳፋሪዎችን በሙሉ ሲገድል በህንፃ ውስጥ የነበሩ 125 ሰዎች ሞተዋል፣ የህንፃውም መዋቅር በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
አራተኛው አውሮፕላን ከኒውአርክ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ ተነስቶ ምን አልባት ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ወይም ወደ ነጩ ቤተመንግሥት እየተጓዘ ነበር፡፡ ነገር ግን ተጓዦች አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ታገሉ፤ በእነዚህ ጀግኖች ዜጎች ምክንያት፣ አሸባሪዎቹ ግባቸው ሊሳካ አልቻለም፤ አውሮፕላኒ በሻክስቪል ፔንሲልቫኒያ አካባቢ ተከስክሶ ተሳፍረው የነበሩት ሁሉም 40 ሰዎች ሞተዋል፡፡
እነዚህ ጥቃቶች በ1941 በፐርል ኸርበር ከተፈፀመው ጥቃት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ በውጭ ሀይል የተፈፀመ ከፍተኛው ጥቃት ነው፡፡
