ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) ተብሎ የሚታወቀውን ሽብርተኛ ድርጅት የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) ዋና መቀመጫው የመን ሲሆን፣ በልዩ ልዩ የፋይናንስ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ገንዘብ ያገኛል፡፡ ከእነርሱም መካከል ገንዘብ ብዝበዛ፣ ሕገወጥ የነዳጅ ዝውውር እና ሽያጭ እንዲሁም በወጭ አገር ከሚገኙ ገንዘብ ረጂዎቹ የሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ይገኙባቸዋል፡፡ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) መሪዎች በዚህ መልኩ የሚያገኙትን ገንዘብ ለጦር መሣሪያ ግዢ፣ ለሥልጠና እንዲሁም ለሽብር ድርጊቶች እና የየመንን ግዛቶች ለመቆጣጠር ተጠቅመዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የየአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) የገቢ ምንጮች እና ቁልፍ የፋይናንስ ማሳለጫ ዘዴዎቹን ለመለየት እና ለማዛባት የሚያስችል መረጃ ለሚሰጡ ወሮታ ይከፈላል፤ መረጃው ከሚመለከታቸውም መካከል፡-
- ስለአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ በመሆን በዓለም ዓቀፍ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሰማሩ ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች፤
- የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የዩናይትድ ስቴትስን እና የዓለም ዓቀፍ ማዕቀቦችን ለመጣስ የሚያስችሉት ተቋማት ወይም ግለሰቦች፤
- ከአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ጋር ይፋዊ የፋይናንስ ተቋማት፤
- ለአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የሚደረጉ የገንዘብ እና የማቴሪያል ማስተላለፍ፤
- የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ገንዘብ ረጂዎች ወይም የፋይናንስ ተቋማት፤
- ለአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የገንዘብ ልውውጥ የሚያመቻቹ የፋይናንስ ተቋማት ወይም የልውውጥ ቤቶች፤
- በአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ እና በእርሱ ገንዘብ ረጂዎች ባለቤትነት ስር ያሉ የንግድ ድርጅቶች ወይም ኢንቬስትመንት፤
- በአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ወይም እርሱን ለመጥቀም ኢንተርኔት አማካኝነት የሚካሄዱ ገንዘብ የማሰባሰብ ዘመቻዎች፤
- በአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ገንዘብ ለማስተላለፍ እና ለመነገድ ጥቅም ላይ የሚውሉ የፋይናንስ የሒሳብ ቁጥሮች ወይም ቨርቹዋል ከረንሲ ዋሌት አድራሻዎች፤ እና
- የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ አባላት እና ደጋፊዎቻቸው የሚሳተፉባቸው እና ድርጅቱን በገንዘብ የሚጠቅሙ የወንጀል መዋቅሮች ወይም ተግባራት፡፡
የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የየመን እና የሳውዲ የሽብር ኃይሎች ከተዋሃዱ በኋላ በጥር 2001 የተመሠረተ ነው፡፡ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ካስመጣቸው ግቦች መካከል፡- በአረብ ባሕረ ሰላጤ እና በሰፊው መካከለኛው ምሥራቅ እስላማዊ መንግሥት ወይም ካሊፌት መመስረት እና የሸሪዓ ሕግን ተግባራዊ ማድረግ አንዱ ነው፡፡ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ በአረብ ባሕረ ሰላጤ ውስጥ አካባቢያዊ፣ የዩናይትድ ስቴትስን እና የምዕራቡን ዓለም ጥቅሞች ዒላማ አድርጓል፡፡ ይህ ቡድን ለበርካታ የሽብር ጥቃቶች ኃላፊነት የወሰደ ሲሆን ከእነርሱም መካከል በጥር 2007 ዓ.ም. በፓሪስ ውስጥ በቻርሊ ሄብዶ የጋዜጣ አሳታሚ መሥሪያ ቤት ላይ የተፈጸመውን እና የ12 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ጥቃት ይገኝበታል፡፡
የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የአል-ቃዒዳ ተባባሪ የሽብር ድርጅት ነው፤ ከአል-ቃዒዳ ዓለም ዓቀፍ አመራር ጋር በመስራት የምዕራቡን ዓለም ዒላማ አድርጎ ይሰራል፤ ከሌሎች ተባባሪ ድርጅቶችም ጋር ያለውን ትብብር ያጠናክራል፡፡ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ቁልፍ እሴት ከአል-ቃዒዳ ሰፊ ኔትወርክ ጋር ያለው የፋይናንስ እ የማሳለጥ ግንኙነት ነው፡፡
የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ በታኅሳስ 16 ቀን 2002 ዓ.ም. ኡመር ፋሩቅ አብዱልሙጠሊብ የተባለ አሸባሪ በሰውነቱ ላይ በታሰረ ቦምብ አንድን አውሮፕላን ለማውደም ቢሞክርም ሙከራው አልተሳካም፡፡ እንዲሁም ይህ ቡድን በ2002 ዓ.ም. መጨረሻ በሁለት የጭነት አውሮፕላኖች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመጓጓዝ በነበሩ ፕሪንተሮች ውስጥ ፈንጂዎች ደብቆ ነበር፤ አውሮፕላኖቹ በሁለት ስፍራዎች ሲያርፉም ቦምቦቹ በጥቅምት 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ተገኝተው ጉዳት አላደረሱም፡፡
በጥር 11 ቀን 2002 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት እንዲሁም ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው ሰይሞታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከየአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም ለኤኪውአይኤስ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
