ሱባይት ቢን ሃሪት

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በየመን የሚንቀሳቀሰው የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) ተብሎ የሚታወቀውን ሽብርተኛ ድርጅት የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

ሱባይት ቢን ሃሪት ከፍተኛ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ መሪ እና የዚህ ቡድን የሹራ ምክር ቤት አባል ነው፡፡

ይህ ግለሰብ በሌላ ስሙ አቡ ጋዛዋን አል-ሃድራሚ ተብሎ ይጠራል፤ ግለሰቡ የቡድኑን የፋይናንስ እንቅስቃሴ ከመምራቱም ባሻገር የውጭ አገር ዜግነት ያላቸውን ተዋጊዎች ጉዞ አስተባብሯል፡፡

Skip to content