አምር ከማል ሸሪፍ አልሳዋ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ሐማስ ተብሎ የሚታወቀውን ሽብርተኛ ድርጅት ወይም በሌላ ስሙ ሃረካት አል-ሙቃዋማ አል-ኢስላሚያ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

አምር ከማል ሸሪፍ አልሻዋ በቱርክ የሚገኘው ከሐማስ ጋር ግንኙነት ያለው ጂዋይኦ በመባል የሚታወቀው የኢንቬስትመንት ፈንድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነው፡፡ በልዩ ልዩ ሐማስ የኢንቬስትመንት ድርጅቶች ውስጥ በቦርድ አባልነት ሰርቷል፡፡

በ2010 ዓ.ም. የሐማስ ኃይሎች ከጂዋይኦ አክሲዮኖች መካከል 75 በመቶ የሚሆነውን በባለቤትነት ይዘው ነበር፡፡ በተጨማሪም፣ ሃማስ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዋጋ ያለውን አክሲዮን ለዚህ ኢንቬስትመንት የበላይ መሪዎች በምስጢር ለመስጠት ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ (ኤግዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224፣ እንደተሻሻለው አልሻዋን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት ሰይሞታል፡፡ በዚህ መልኩ መሰየሙም የሽብር ጥቃት በሚፈጽሙ ወይም ከፍተኛ የመፈጸም ዕድል ያላቸውን የውጭ አገር ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች ላይ ዕግድ ይጥላል፡፡ ከዚህም ሌላ ይህ ትዕዛዝ የዩይነትድ ስቴትስ መንግሥት በዚህ ትዕዛዝ ስር ሽብርተኞች እና የሽብር ድርጅቶች ተብለው ለተሰየሙት ወይም ለእነርሱ የበታች ድርጅቶች፣ ሽፋን ሰጪዎች፣ ወኪሎች ወይም ተባባሪዎች ድጋፍ፣ አገልግሎቶች ወይም እገዛ የሚሰጡትን ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች እንዲያግድ የሚያዝ ነው፡፡

Skip to content