አሕመድ ሳዱ ካህሌብ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ሐማስ ተብሎ የሚታወቀውን ሽብርተኛ ድርጅት ወይም በሌላ ስሙ ሃረካት አል-ሙቃዋማ አል-ኢስላሚያ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

አሕመድ ሳዱ ጃህለብ የሐማስ አባል ሲሆን፣ በቱርክ የሐማስ ኢንቬስትመንት ሥራዎች አባል ነው፡፡ ጃህለብ የሐማስ የኢንቬስትመንት ጸሐፊ በመሆን በመስራት ላይ ሲሆን፣ በሐማስ ቁጥጥር ስር ያሉ ኩባንያዎችን እና የሐማስን የሥራ ኃላፊዎች ሥራ ልዩ ልዩ እንቅስቃሴዎች አስተባባሪ እና ጸሐፊ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት 07 ቀን 2016 ዓ.ም. ጃህላብን በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ (ኤግዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224፣ እንደተሻሻለው ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት ሰይሞታል፡፡ በዚህ መልኩ መሰየሙም የሽብር ጥቃት በሚፈጽሙ ወይም ከፍተኛ የመፈጸም ዕድል ያላቸውን የውጭ አገር ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች ላይ ዕግድ ይጥላል፡፡ ከዚህም ሌላ ይህ ትዕዛዝ የዩይነትድ ስቴትስ መንግሥት በዚህ ትዕዛዝ ስር ሽብርተኞች እና የሽብር ድርጅቶች ተብለው ለተሰየሙት ወይም ለእነርሱ የበታች ድርጅቶች፣ ሽፋን ሰጪዎች፣ ወኪሎች ወይም ተባባሪዎች ድጋፍ፣ አገልግሎቶች ወይም እገዛ የሚሰጡትን ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች እንዲያግድ የሚያዝ ነው፡፡

Skip to content