አቡካር አሊ አደን

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

አደን የአልሸባብ ምክትል መሪ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ጃባህት ተብሎ የሚታወቀውን የአልሸባብ ወታደራዊ ክንፍ ለበርካታ አመታት ሲመራ ቆይቷል፡፡

በጥር 2010 ዓ.ም. የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቡካር አሊ አደንን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት በሥራ አስፈጻሚ ትእዛዝ ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 መሠረት ሰይሞታል፤ በዚህም ትዕዛዝ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ወይም ብሔራዊ ደህንነትን፣ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ወይም ኢኮኖሚ ላይ የሽብር ጥቃት የፈጸሙ ወይም ለመፈጸም ከፍተኛ ዕድል ባላቸው ላይ ጥብቅ ማዕቀብ ይጥላል፡፡ እንዲሁም ይህ ግለሰብ በትባበሩት መንግሥታት ውሳኔ 1844 (2000 ዓ.ም.) መሠረት በሶማሊያ እና በሰላም አስከባሪዎች ሰላም፣ ደህንነት ወይም የተረጋጋ ተግባር ላይ ስጋት በሚደቅኑ አካላት ዝርዝር ውስጥ ተካትቶ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አደን ከአል-ቃዒዳ ተባባሪ ድርጅቶች፣ ከአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ እና አል-ቃዒዳ በኢስላሚክ ማግሪብ ጋር ግንኙነት አለው፡፡

 

Skip to content