Success stories

ሃማሲራጂ ሙሪሳይ ሳሊ (ሞቷል)

በፊሊፒንስ የአሜሪካዊያን መታፈን እና ግድያ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ አቡ ሳያፍ ግሩፕ (ኤኤስጂ) ኮማንደር ሃምሲራጂ ሳሊ መገኛ መረጃ ለሰጠ $1 ሚሊዮን ወሮታ ከፍሏል፡፡

ሃምሲራጂ ሳሊ በነሐሴ 22 ቀን 1992 ዓ.ም. በኤኤስጂ በአሜሪካ ዜጋ ጄፍሪ ሺሊንግ አፈና እንዲሁም በግንቦት 19 ቀን 1993 ዓ.ም. በተፈጸመው የዶስ ፓልማስ የአፈና ተሳትፏል፡፡ ጄፍሪ ሺሊንግን ለመልቀቅ ኤኤስጂ $10 ሚሊዮን እንዲከፈለው እና በአሜሪካ እስር ቤቶች የሚገኙ ሦስት ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኞች ከእሰር እንዲፈቱ ጠየቀ፡፡ እንዲለቀቁ የተጠየቁትም የአል-ቃዒዳ አባላት፡- ራምዚ ዮሱፍ፣ ዋሊ ኻን እና የግብጽ ሽብርተኛ ቡድን አል-ጋማዓት አል-ኢስላሚያ መሪ ኦማር አብድ አል-ራህማን (በሌላ ስሙ “ዓይነ ስውሩ ሼህ”) ነበሩ፡፡

በሚያዝያ 04 ቀን 1993 ዓ.ም. የፊሊፒንስ የጦር ኃይል ጄፍሪ ሺሊንግ ታግቶ በነበረበት በኤኤስጂ ካምፕ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት ለማምለጥ እና በኋላም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመመለስ ችሏል፡፡

በግንቦት 19 ቀን 1993 ዓ.ም. ኤኤስጂ በፓላዋን፣ ፊሊፒንስ በዶስ ፓልማስ ሪዞርት ሦስት አሜሪካዊያንን አፈነ፡፡ ሦስቱ አሜሪካዊያንም ጉዊሌርሞ ሶቤሮ እና የዩናይትድ ስቴትስ ሚሲዮን አባላት የትዳር አጋሮቹ ማርቲን እና ጋርሲያ በርንሃም ነበሩ፡፡ በሰኔ 04 ቀን 1993 ዓ.ም. የኤኤስጂ ቃል አቀባይ አቡ ሳያፍ፣ ጉዊሌርሞ ሶቤሮ ለፊሊፒንስ ፕሬዚደንት ግሎሪያ ማካፓጋል-አሮዮ የልደት ስጦታ እንዲሆን መገደሉን ገለጸ፡፡ በመስከረም 27 ቀን 1994 ዓ.ም. በባዚላን ደሴት የሰው አጽም ጭንቅላት ተገኘ፤ ይህ ጭንቅላት የሟች ጉዊሌርሞ ሶቤሮ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ በሰኔ 1994 ዓ.ም. ማርቲን በርንሃም በፊሊፒንስ ወታደሮች እና በኤኤስጂ መካከል በነበረው የተኩስ ልውውጥ ተገደለ፤ ጋርሲያ በርንሃም ብትቆስልም ለመትረፍ እና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመመለስ ችላለች፡፡

በየካቲት 1994 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ ግራንድ ጁሪ ከዚህ በሚከተሉት ጭብጦች በሳሊ ላይ ክስ እንዲመሰረትበት ወስኗል፡- ሞትን ያስከተለ መመሳጠር፣ ሞትን ያስከተለ እገታ – ሦስት የእገታ ክሶች፡፡ በመጋቢት 30 ቀን 1996 ዓ.ም. የፊሊፒንስ ጦር ኃይል በተለያዩ መረጃ ሰጪዎች በደረሰው መረጃ መሠረት ሳሊን ለመያዝ ኦፕሬሽን አካሂዶ በዚህ ወቅት ከወታደሮች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሳሊ ተገድሏል፡፡

Skip to content