Success stories

አቡ ሶላይማን (ሞቷል)

በፊሊፒንስ የአሜሪካዊያን መታፈን እና ግድያ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ አቡ ሳይፍ ቡድን (ኤኤስጂ) መሪ አቡ ሶለይማን መረጃ ለሰጡ ሁለት ግለሰቦች $5 ሚሊዮን ወሮታ ከፍሏል፡፡ በግንቦት 30 ቀን 1999 ዓ.ም. በፊሊፒንስ የአሜሪካ አምባሳደር በዚህ በጆሎ ደሴት በተካሄደው ይፋዊ የወሮታ አከፋፈል ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል፡፡

አቡ ሶለይማን ከኤኤስጂ ከፍተኛ አመራር አባላት መካከል አንዱ ነበር፤ ከኻዳፋይ ጃንጃላኒ ጋር በአንድነት በመሆን ለፊሊፒንስ እና የአሜሪካ ዜጎች መታፈን እና ሞት በኃላፊነት ይጠየቃል፡፡ ሶለይማን ለማርቲን እና ጋርሲያ በርንሃም እና በሁለት ሌሎች የአሜሪካ ዜጎች መታፈን ጋር ግንኙነት አለው፤ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ በሆነው ጉዊሌርሞ ሶቤሮ መቀላት ላይ ተሳትፎ ነበረው፡፡ በተጨማሪም ሶለይማን የዩናይትድ ስቴትስን ጥቅሞች ዒላማ ያደርጉ ጥቃቶች ለምሳሌ በማኒላ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ላይ የቦምብ ጥቃት ለመፈጸም ሲካሄድ የነበረ ሴራ፣ በየካቲት 1996 ዓ.ም. የሱፐርፌሪ 14 መስጠም እና የ1997 ዓ.ም. የቫለንታይን ቀን ሦስት የቦምብ ጥቃቶችን ያቀደ እና ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፣ በእነዚህም በድምሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል ወይም ቆስለዋል፡፡

በጥር 08 ቀን 1999 ዓ.ም. የፊሊፒንስ የጦር ኃይል በመረጃ ሰጪዎች ባገኘው መረጃ ላይ በመመስረት ሶላይማንን ለመያዝ ኦፕሬሽን አካሄዱ፤ በዚህም እንቅስቃሴ ወቅት ሶላይማን ለመቋቋም በመሞከሩ ምክንያት ተገድሏል፡፡

Skip to content