ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ዘሪን ሳሪ፣ በሌላ ስሟ ፋጢማ ጉልተን እና ሃሌ መሊስ መረጃ ለሚስጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሳሪ በዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተሰየመው እና ከ1980ዎቹ ጀምሮ በቱርክ መንግሥት ተቋማት እና በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ተቋማት ላይ ጥቃቶች ሲፈጽም የቆየው የሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ሊበሬሽን ፓርቲ/ፍሮንት (ዲኤችኬፒ/ሲ) ቁልፍ መሪ ናት፡፡ የዚህ ድርጅት ግብ ከቱርክ ዩናይትድ ስቴትስን እና ኔቶን ማስወጣት እና ኅብረተሰባዊት ቱርክን መመስረት ነው፡፡
ሳሪ ለነበራት እንቅስቃሴ ምክንያት ታስራ ነበር፤ ነገር ግን የዲኤችኬፒ/ሲ መስራት አባል የነበረው የባለቤቷ ዱርሱን ካራታስ ሞት ተከትሎ ከእስር ተለቃ ነበር፡፡ በመጋቢት 2005 ዓ.ም. በጀስቲስ ኤንድ ዲቨሎፕመንት ፓርቲ (ኤኬፒ) ዋና መሥሪያ ቤት እና በቱርክ የፍትሕ ሚኒስቴር ላይ በአንካራ ለተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች ተብሎ ይታመናል፤ በተመሳሳይ መልኩ በመስከረም 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በቱርክ ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት እና በአንካራ የፖሊስ መኖሪያ ቤቶች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች ተብሎ ይታመናል፡፡
