ያሲን ኪልዌ

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 3 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተሰየመው አልሸባብ ክልላዊ መሪ ያሲን ኪልዌ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ያስሚን ኡስማን ኪልዌ እና ያሲን ኻሊድ ኦስማን፣ ኪልዌ በሰሜን ሶማሊያ የፑንትላንድ የአል-ሸባብ መሪ እና በፑንትላንድ መሪዎች ላይ ጥቃቶችን በማቀድ ክስ ይቀርብበታል፡፡

አል-ሸባብን ከመቀላቀሉ በፊት ኪልዌ በሰሜን ሶማሊያ የጋልጋላ ሂልስ የአካባቢ ሚሊሽያ መሪ ነበር፡፡ ይህ ሚሊሽያ በአቀበታማው አካባቢ ያሉ ግዛቶችን ይዟል፤ በአካባቢው በሚገኝ ወታደራዊ ሰፈርም ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡

በ2004 ዓ.ም. የኪልዌ ሚሊሽያ በይፋ ከአልሸባብ ጋር ተቀላቀለ፤ ይህም በተመሳሰይ ወር ለአል-ቃዒዳ (ኤኪው) ታማኝ መሆኑን ገለጸ፡፡ ይህ ውህደት ለአል-ሸባብ እና በመቀጠልም ለአል-ቃዒዳ ከፍተኛ የውጊያ ኃይል ሰጥቶታል፡፡

Skip to content