ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ዳዋዉድ ሙሐመድ ሃፊዝ አል-ቱርኪ፣ በሌላ ስሙ ስሊማን አሊ አሕመድ ኤል-ቱርኪ እና ቦዉ ባከር ሙሐመድ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ቱርኪ የአቡ ኒዳል ሽብርተኛ ቡድን አባል ነው የተባለ ሲሆን፣ በነሐሴ 30 ቀን 1978 ዓ.ም. በካራቺ፣ ፓኪስታን በተፈጸመው የፓን አም የበረራ 73 ጠለፋ ለነበረው ሚና ተፈላጊ ነው፡፡ 379 ተሳፋሪዎችን እና የበረራ ሠራተኞችን ለ16 ሰዓታት ያህል አግተው ካቆዩ በኋላ፣ አጋቾቹ በጭፍን ተኩስ ከፈቱ፤ በዚህም ሁለት አሜሪካዊያንን ጨምሮ ሃያ ሰዎች ሲሞቱ፣ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡
በጠለፋው ላይ ለነበረው ተሳትፎ ራሂም በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ግራንድ ጁሪ የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል ውሳኔ የተሰጠበት ሲሆን፣ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተካቷል፡፡ አል-ቱርኪ በምኅንድስና የሰራ፣ በበዛ ደረጃ ሲጋራ አጫሽ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ነዋሪ ነው፡፡
