በዩኤስኦ ክለብ የቦምብ ጥቃት

አውሮፓ እና ዩራሺያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በኔፓልስ፣ ጣሊያን በዩኤስኦ ክለብ ላይ ስለተፈጸመው የቦንብ ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በሚያዝያ 06 ቀን 1980 ዓ.ም. በተጠቀሰው ስፍራ ፊት ለፊት ቦምብ ፈንድቶ የዩናይትድ ስቴትስ ሴት ወታደርን ጨምሮ አምስት ሰዎችን ለሞት ሲዳርግ አራት ወታደሮችን ጨምሮ ሌሎች 15 ሰዎች ላይ ጉዳት አስከትሏል፡፡

ጁንዞ ኦኩዳሪያ፣ የጃፓን ቀይ ሠራዊት (ሬድ አርሚ) ተብሎ የሚጠራው ሽብርተኛ ድርጅት አባል ሲሆን፣ በሚያዝያ 01 ቀን 1985 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ ስለተፈጸመው ጥቃት ክስ እንዲመሰረትበት ተወስኗል፡፡ እንዲሁም ኦኩዳሪያ በሰኔ 1979 ዓ.ም. በሮም በዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ላይ ለተፈጸመው የቦምብ እና የሞርታር ጥቃት ተጠርጣሪ ነው፡፡

Skip to content