የቲደብልዩኤ በረራ 847 ጠለፋ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | አውሮፓ እና ዩራሺያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በ1977 ዓ.ም. በበረራ 847 ላይ ስለተፈጸመው ጠለፋ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በሰኔ 07 ቀን 1977 ዓ.ም. በበረራ 847 ከአቴንስ ወደ ሮም በመጓዝ ላይ ሳለ በሽብርተኞች ተጠልፏል፡፡ ለ17 ቀናት አውሮፕላኑ 153 ተሳፋሪዎች እና የበረራ ሠራተኞች ይዞ ከቤይሩት ወደ አልጀርስ እና እንደ ገና ተመልሶ ወደ ቤይሩት በመጓዝ ሜዲትራኒያንን ለሦስት ጊዜያት እንዲያቋርጥ ተገዷል፡፡ መጀመሪያ ቤይሩት ሲያርፍ፣ ጠላፊዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ሾፌር የነበረውን ሮበርት ስቴተም ክፉኛ በመደብደብ ገድለዋል፡፡

በኅዳር 05 ቀን 1978 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ግራንድ ጁሪ አሊ አትዋ፣ መሐመድ አሊ ሃማዴይ እና ሃሰን ኢዝ-አል-ዲን በጠለፋው ላይ ስለነበራቸው ተሳትፎ ክስ እንዲመሰረትባቸው ወስኗል፡፡ ወሮታ ለፍትሕ ስለ አትዋ፣ ሃምዳይ እና ኢዝ-ዲን መረጃ ለሚሰጥ ለእያንዳንዳቸው $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

Skip to content