ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በዳካ፣ ባንግላዴሽ በቪት ሮይ ላይ ስለተፈጸመው ግድያ እና በዚያውም በራፊዳ ቦንያ አሕመድ ላይ ስለተፈጸመው ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
በየካቲት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. የባንግላዴሽ ተወለዳጅ አሜሪካዊያን ዜጎች ባልና ሚስት ሮይ እና አሕመድ በዳካ ተገኝተው በአንድ የመጽሐፍት ሽያጭ ላይ ሳሉ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች በማጭድ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ ሮይ በማጭዱ በደረሰበት ጥቃት ሲሞት፣ አሕመድ ደግሞ በጣቱ እና በጭንቅላቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
ሮይ ጸሐፊ፣ ብሎገር እና አክቲቪስት እንደመሆኑ መጠን፣ ለንግግር ነጻነት በመታገል በባንግላዴሽ አክራሪነትን ፈትኗል፡፡ በባንግላዴሽ ለእስር ስለተዳረጉ ኢአማኒያን ብሎገሮች ግንዛቤ ለመፍጠር ዓለም ዓቀፍ ተቃውሞዎችን አደራጅቷል፤ የማኅበራዊ ጭቆና ተቃዋሚ ለመሆኑም ታዋቂነትን አትርፏል ነው፡፡ ስለ ይፋዊ እምነቶቹ እና ማኅበራዊ አንቂነቱ ዒላማ ተደርጎ ተገድሏል፡፡
አንሳሩላህ ባንግላ ቡድን (ኤቢቲ) የተባለው የባንግላዴሽ የሽብር ቡድን ለዚህ ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡ ኤቢቲ ጸረ ኢስላም ናቸው የሚባሉት ላይ ግድያ እንዲፈጽሙ ወጣቶችን አክራሪ የማድረግ ፍላጎት አለው፡፡ ይህ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ አሲም ኡመር፣ በአሁኑ ጊዜ በሞት የተለየ የሕንድ ንዑስ አሕጉር የአልቃዒዳ (ኤኪውአይኤስ) መሪ የዚህ ቡድን ተከታዮች፣ ወደፊት በቁጥጥር ስር የሚውሉትን ጨምሮ በሮይ እና አሕመድ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ፈጻሚዎች መሆናቸውን በማመን በሰፊው የተሰራጨ ቪድዮ ለጥፈዋል፡፡
በሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕንድ ንዑስ አሕጉር የአልቃዒዳ (ኤኪውአይኤስ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ሲል በሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤኪውአይኤስን ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የኤኪውአይኤስ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከኤኪውአይኤስ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም ለኤኪውአይኤስ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
ለጥቃቱ ተጠያቂ የሆኑት ባንግላዲሽ ውስጥ ይገኛሉ ተብሎ ይታመናል፡፡
