ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ታላል ሃሚያህ በሌላ ስሙ ኢስማት መዛራኒ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $7 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሃሚያህ የሂዝባላ ውጫዊ ደህንነት ድርጅት (ኢኤስኦ) ኃላፊ ሲሆን፣ ይህ ድርጅት በዓለም ዙሪያ ሕዋሳት አሉት፡፡ ኢኤስኦ ከሊባኖስ ውጪ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የማቀድ፣ የማስተባበር እና የመፈጸም ኃላፊነት ያለው የሂዝባሃል አካል ነው፡፡ ጥቃቶቹ በዋናነት እስራኤላዊያን እና አሜሪካዊያንን ኢላማ ያደረጉ ናቸው፡፡
በመስከረም 03 ቀን 2005 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ሃሚያህን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሃሚያህ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሃሚያህ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
