ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሳሚ ጃሲም ሙሐመድ አል-ጃቡሪ፣ በሌላ ስሙ ሐጂ ሐሚድ እና ሳሚ ጃሚስ ሙሐመድ አል-ዓጁዝ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ጃቡሪ የኢራቅ እና ሶሪያ ኢስላማዊ መንግሥት (አይሲስ) ከፍተኛ አመራር ሲሆን፣ አስቀድሞ ደግሞ የአይሲስ አስወራሽ የነበረው አል-ቃዒዳ በኢራቅ አባል ነበር፡፡ አል-ጃቡሪ የአይሲስን የሽበር ሥራዎች ፋይናንስ በመምራቱ ረገድ ጠቃሚ ሰው ነበር፡፡
አል-ጃቡሪ በ2006 ዓ.ም. በደቡብ ሞውሱል የአይሲስ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግል፣ ከአይሲስ የፋይናንስ ሚኒስቴር ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ኃላፊነት ነበረው ተብሏል፤ በዚህም መልኩ በሕገወት የነዳጅ፣ ቅርሳቅርስ እና ማዕድናት ሽያጭ የቡድኑን የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች ይመራ ነበር፡፡
በመስከረም 18 ቀን 2008 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አል-ጃቡሪን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ጃቡሪ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ጃቡሪ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አይሲስ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
