ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሳልማን ራዉፍ ሳልማን በሌላ ስሙ ሳሙኤል ሳልማን ኤል ረዳ እና ሳልማን ሬማል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $7 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሳልማን የሂዝባላህን የምዕራብ መንፈቀ ዓለም የሽብር እንቅስቃሴዎች ይመራል እንዲሁም ይደግፋል፡፡ የሂዝባላህ የውጪ ደህንነት ድርጅት (ኢኤስኦ) መሪ የሆነው ሳልማን በዓለም ዙሪያ በሚፈጸሙ ሴራዎች ሲሳተፍ ቆይቷል፡፡ ኢኤስኦ ከሊባኖስ ውጪ የሚፈጸሙ የሂዝባላህ የሽብር ጥቃቶች ዕቅድ አውጪ፣ አስተባባሪ እና ፈጻሚ ነው፡፡ ጥቃቶቹ በዋናነት አሜሪካዊያንን እና እስራኤላዊያንን ዒላማ ያደረጉ ናቸው፡፡
ሳልማን በቦነስ አይረስ በሚገኘው የአርጀንቲና የአይሁድ ማኅበረሰብ ማዕከል ላይ በሐምሌ 11 ቀን 1986 ዓ.ም. የተፈጸመው የቦምብ ፍንዳታ ጥቃት አስተባባሪ ነው ተብሏል፡፡ ይህ ቦምብ በተሽከርካሪ ላይ ተመሳስሎ የተጠመደ ነበር፤ በፍንዳታውም 85 ሰዎች ሲሞቱ፣ 300 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በሐምሌ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ሳልማንን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሳልማን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሳልማን ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
