የፓን አም የበረራ 103 የቦምብ ፍንዳታ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | አውሮፓ እና ዩራሺያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ፓን አም የበረራ 103 የቦምብ ፍንዳታ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በታኅሳስ 12 ቀን 1981 ዓ.ም. በፓን አም በረራ 103 ቦይንግ 747 ከለንደን ሄዝሮው አየር ማረፊያ ወደ ኒው ዮርክ ጆን ኤፍ. ኬኔዲ አየር ማረፊያ በመብረር ላይ ነበር፡፡ አውሮፕላኑ በበረራ ላይ ሳለ በሻንጣ ውስጥ ተደብቆ የነበረ የተመሳሰለ ፈንጂ ፈንድቶ አውሮፕላኑ በሎከርቤ፣ ስኮትላንድ ወድሟል፡፡ ይህ ፍንዳታ 259 ተጓዦች እና የበረራ ሠራተኞችን ገድሏል፤ ከሟቾች መካከል 190 አሜሪካዊያን ዜጎች ነበሩ፤ በተጨማሪም በመሬት ላይ 11 ነዋሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ይህ ጥቃት የታቀደው እና የተፈጸመው በሊቢያዊያን የቀድሞ የደህንነት ሠራተኞች ነበር፤ ይህ ጥቃት ከመስከረም 01 ቀን 1994 ዓ.ም. ጥቃት በፊት በአሜሪካ ላይ የተፈጸመ ከፍተኛው ጥቃት ነበር፡፡ ይህ ጥቃት በዩናይትድ ኪንግደም ላይ የተፈጸመው የበርካታ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈ ከፍተኛው ጥቃት ነው፡፡

ጥፋቱ ከተከሰተ በኋላ ወዲያውኑ የስኮትላንድ እና የአሜሪካ ሕግ አስከባሪዎች በጋራ ምርመራ አካሄዱ፡፡ በኅዳር 1984 ዓ.ም. ዩናይትድ ስቴትስ እና ስኮትላንድ በሊቢያ የደህንነት ሠራተኞች አብደል ባሴጥ አሊ አል-መግራሂ እና ላሜን ኸሊፋ ፊማህ ላይ የወንጀል ክስ መሠረቱ፡፡

በጥር 23 ቀን 1993 ዓ.ም.፣ አል መግራሂ ሁሉንም ክሶች እንዲከላከል ሲበየንበት፣ በፊማህ ላይ የቀረበው ክስ ግን ውድቅ ተደርጓል፡፡ አል-መግራሂ የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈረደበት፡፡ ግለሰቡ ለሞት የሚዳርግ ካንሰር ከተገኘበት በኋላ በሰብዓዊ ሃዘኔታ በነሐሴ 2001 ዓ.ም. ከእስር ተለቋል፡፡ አል-መግራሂ በግንቦት 2004 ዓ.ም. በመኖሪያ ቤቱ ከዚህ ዓለም በሞተ ተለይቷል፡፡

በታኅሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የፍትሕ ሚኒስቴር የቀድሞ የሊቢያ የደህንነት ሠራተኛ አቡ አገላ ማስዑድ ኸይር አል-ማሪሚ በቦምብ ጥቃቱ ላይ ለነበረው ተሳትፎ አዲስ ክስ መስርቶበታል፡፡

Skip to content