የጆን ግራፊል እና የአብደልራህማን አባስ ራህማ ግድያ

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም ዓቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤድ) ሠራተኞች ጆን ግራቪል እና አብደልራህማን አባስ ራሃማ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በታኅሳስ 22 ቀን 2000 ዓ.ም. ግራቪል እና ራሃማ በካርቱም ከተማ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ፓርቲ ላይ ተገኝተው ወደ የቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ በጥይት ተመትተው ተገድለዋል፡፡ ለግድያዎቹ ሁለት ቡድኖች በየራሳቸው ኃላፊነት ወስደዋል፤ እነርሱም፡- በአሁኑ ጊዜ ከተግባር ውጪ የሆነው አል-ቃዒዳ በሁለቱ ናይሎች (አል ቃዒዳ ኢን ዘ ቱ ናይልስ) (ኤኪውቲኤን) እና አንሳር ታውሂድ (የእምነት በአንድ ፈጣሪ ደጋፊዎች) ናቸው፡፡

በእነዚህ ገድያዎች በነበራቸው ተሳትፎ አምስት ሰዎች በሱዳን የፍርድ ሥርዓት ጥፋተኞች ተብለዋል፤ አብደልራዉፍ አቡ ዛይድ መሐመድ ሐምዛ፣ መሐመድ ማቃዊ ኢብራሂም መሐመድ፣ አብደልበሲጥ አልሃጅ አልሃሰን ሃጅ ሃማድ እና ሞሃናድ ኦስማን ዩሱፍ መሐመድ በስቅላት እንዲቀጡ ቢፈረድባቸውም፣ ጥፋተኞች በተባሉ በአንድ ዓመቱ ከእስር ቤት አምልጠዋል፡፡ ሞሃናድ በግንቦት 2003 ዓ.ም. በሶማሊያ ውስጥ ሞቷል ተብሏል፡፡ አብደልራዉፍ በሱዳን ባለሥልጣናት በድጋሚ ሊያዝ ችሏል፡፡ ማቃዊ አብድልበሲጥ እስከ አሁን አልተያዙም፡፡ [ስለ ማቃዊ እና አብደልበሲጥ የቀረቡ ወሮታዎች ሃይፐርሊንክ] ጆን ግራቪል በካሜሩን የቀድሞ የሰላም ጓድ በጎ ፈቃደኛ እና ተመራማሪ ነበር፤ ከሦስት ዓመታት በላይ በሱዳን የዩኤስኤይድ ሠራተኛ ሆኖ ሰርቷል፡፡ ሥራውም በዴሞክራሲ እና በመንግሥት አስተዳደር ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር፤ በዚህም ሥራው ዜጎች መብቶታቸውን እንዲጠሙ እና ለምርጫዎች ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ከ50,000 በላይ ሶላር ሬድዮዎችን አከፋፍሏል፡፡ ብደልራህማን አባስ፣ በወቅቱ ዕድሜው 39 ዓመት፣ በዳርፉር፣ ሱዳን የዩናይትድ ስቴትስ የአደጋ እርዳታ ምላሽ ሰጪ ቡድን (ዲዛስተር አሲስታንስ ሪስፖንስ ቲም) አባል ሆኖ 1996 ዓ.ም. ጀምሮ በዩኤስኤድ ይሰራ ነበር፡፡ በኋላ ግን በካርቱም የዩኤስኤድ/ሱዳን ሚሲዮን ሾፌር ሆነ፡፡

Skip to content