ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሙራት ካራይላን በሌላ ስሙ ሴማል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ካራይላን በኩርዲስታን የሠራተኛ ፓርቲ (ፒኬኬ) ከፍተኛ አመራር እና የፒኬኬ መከላከያ ኃይል ኃላፊ ነው፡፡ ፒኬኬ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተሰየመ ድርጅት ነው፡፡
በጥቅምት 04 ቀን 2002 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ካራይላንን በውጭ አገር የናርኮቲክስ ኪንግፒን አሰያየም ሕግ (ኪንግፒን ሕግ) መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ከፍተኛ የናርኮቲክስ አዘዋዋሪ በማለት መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የካራይላን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከካራይላን ጋር የፋይናንስ ወይም የንግድ ልውውጦች ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡
