ሙሃመድ ቃሲ አል-ባዛል

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ የሂዝባላን የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎች ለማሰናከል የሚያስቸል መረጃ ለሚሰጥ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ መሀመድ ቃሲም አል-ባዛል፣ በሌላ ስሙ መሐመድ ባዛል እና ሙዓኢን ቁልፍ የሂዝባላ ባለሥልጣን ሲሆን ከኃላፊነቶቹ መካከል በሂዝባላ እና በኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት- ቆድስ ኃይል (አይአርጂሲ-ኪውኤፍ) መካከል ሒሳብ ማወራረድ ይገኝበታል፡፡

አል-ባዛል በሶሪያ የሚገኘው ታላቂ ቡድን የሚባለው ሽፋን ሰጪ ኩባንያ መሥራቾች መካከል ሲሆን፣ እንደ ሆቆውል ኤስ.ኤ.ኤ. ኦፍሾር እና ናግሃም አል ሃያት ያሉ የሽብር ድርጅቶች ፋይናንስ አቅራቢዎችን ይቆጣጠራል፡፡ የታላቂ ቡድን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር እንደመሆኑ መጠን፣ አል-ባዛል የኩባንያውን ፋይናንስ፣ አሰራር፣ አስተዳደር እና ውሎች በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡ ከ2010 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ አል-ባዛል ታላቂ ቡድንን እና የእርሱን ሌሎች ኩባንያዎች በመጠቀም ልዩ ልዩ ሕገወጥ ከአይአርጂሲ-ጂውኤፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የነዳጅ ጭነቶች በገንዘብ ለመደገፍ፣ ለማስተባበር እና ለመደበቅ ተጠቅሟል፡፡ አል-ባዛል ታላቂ በሊባኖስ ከሚገኘው አሉሚክስ ጋር በመተባበር ወደ ኢራን አሉሚኒየም ለመጫን የሚደረገውን እንቅስቃሴ በበላይነት ተቆጣጥሯል፡፡

በኅዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አል-ባዛልን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ባዛል ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ባዛል ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስቴር በአል-ባዛል ባለቤትነት ወይም ቁጥጥር ስር ያሉትን ሆቆዉል ኤስ.ኤ.ኤል. ኦፍሾር፣ ታላቂ ቡድን፣ ናጋሃም አል ሃያት እና አሉሚክስን በተመሳሳይ መልኩ መዝግቧል፡፡

Skip to content