ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሙሃመድ ካዋታሪኒ በሌላ ስሙ ጃፋር ካዋታሪኒ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ካዋታሪኒ በኢራቅ የሂዝባላ ኃይሎች መሪ ነው፡፡ ካዋታሪኒ በኢራቅ የሚገኘው፣ በሟች ኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ አዛዥ ጀነራል ቃሲም ሶሊማኒ የተደራጁት እና የኢራን ወዳጅ የሆኑ ፓራሚሊተሪ ቡድች ጋር ፖለቲካዊ ማስተባበር ኃላፊነት ይወጣ ነበር፡፡
ካዋታሪኒ ከኢራቅ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ቡድኖችን እንቅስቃሴዎች ያመቻቻል፤ በእነዚህም እንቅስቃሴዎች ኃይል የተሞላባቸው የተቃውሞ ትዕይንቶች ታይተዋል፤ እንዲሁም ሰፊ እና የተደራጁ የወንጀል እንቅስቃሴዎች ላይ ተሳትፎ ተደርጓል፡፡ የሂዝባላ የፖለቲካ ምክር ቤት አባል እንደመሆኑ መጠን ካውታራኒ ሂዝባላ ለኢራቅ ሺዓ ሰርጎገብ ቡድኖች የሥልጠና፣ የገንዘብ፣ የፖለቲካ እና የሎጂስቲከስ ድጋፍ ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት አበረታቷል፡፡ እንዲሁም ካውታራኒ የአሳድን መንግሥት ለማገዝ ወደ ሶሪያ ለሚዘዋወሩ አክራሪዎች እገዛ ሰጥቷል፡፡
በግንቦት 07 ቀን 2010 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ካዋታራኒን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የካዋታራኒ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከካዋታራኒ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
