ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ መሐመድ አሊ ሃማዴይ በሌላ ስሙ አሊ ሃማዴይ እና ካስትሮ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሃማዴይ የሂዝባላ አባል ነው የሚባል ሲሆን፣ በ1977 ዓ.ም. የቲደብልዩኤ በረራ ቁ. 847ን ላይ በተፈጸመው ጠለፋ ላይ ለነበረው ሚና ይፈለጋል፡፡
በሰኔ 07 ቀን 1977 ዓ.ም. ሽብርተኞች ከአቴንስ ወደ ሮም በመብረር ላይ የነበረውን ቲደብሊውኤ በረራ 847 ጠልፈዋል፡፡ ለ17 ቀናት ይህ አውሮፕላን 153 ተጓዦች እና የበረራውን ሰራተኞች ይዞ ከቤይሩት ወደ አልጀርስ እና በድጋሚ ወደ ቤይሩት እንዲጓጓዝ ተገዷል፤ በዚህም መልኩ በቤይሩት ለሶስት ጊዜያት አርፏል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤይሩት ሲያርፍ ጠላፊዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ሀይል አሽከርካሪ የነበረውን ሮበርት ስቴተም ክፉኛ ደብድበው በጥይት መትተው ገድለዋል፡፡
በኅዳር 05 ቀን 1978 ዓ.ም. ሃማዴይ በጠለፋው ላይ ለነበረው ሚና እና ተሳትፎ የቀረበበትን ክስ እንዲከላከል ተበይኖበታል፡፡ በጥር 05 ቀን 1979 ዓ.ም. በፍራንክፈርት አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ይህ ግለሰብ ተላልፎ እንዲሰጥ ብትጠይቅም፣ የጀርመን ፌዴራል ሪፑብሊክ ግን ሃማዴይን በዚያው በጀርመን ውስጥ ለመክሰስ ወስኖ በግንቦት 1981 ዓ.ም. በግድያ፣ በእገታ፣ ጥቃት በመፈጸም እና በአውሮፕላን ጠለፋ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብሏል፡፡ በዚህም ምክንያት የዕድሜ ይፍታህ እስር ተወስኖበት ነበር፡፡ ሆኖም ግን በታኅሳስ 06 ቀን 1998 ዓ.ም. ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ወደ ቤይሩት አቅንቷል፤ አሁንም በዚያ ይገኛል ተብሎ ይታመናል፡፡
በጥቅምት 02 ቀን 1994 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃማዴይን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሃማዴይ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከባዚ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ ሃማዴይ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡
