ማሃድ ካራቴ

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

Up to $10 million

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ማሃድ ካራቴ፣ በሌላ ስሙ አብዲራህማን መሐመድ ዋርሳሜ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ካራቴ በይፋ ያልተገለጠ የአልሸባብ ምክትል አስተዳዳሪ ሆኖ በመስራት ላይ ነው፡፡ ካራቴ አምኒያት ተብሎ በሚጠራው የአልሸባብ የስለላ እና ደህንነት ክንፍ እንዲሁም በቡድኑ ፋይናንስ ጉዳዮች ውስጥ የአዛኝነት ኃላፊነት አለው፡፡

አምኒያት በሶማሊያ፣ ኬኒያ እና ሌሎች በቀጠናው በሚገኙ አገራት ላይ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች እና ግደያዎች በማስፈተሙ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፤ እንዲሁም ይህ ተቋም ለአልሸባብ የሽብር እንቅስቃሴዎች የሎጂስቲክ እገዛ ይሰጣል፡፡ አምኒያት በኬኒያ በጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ላይ ለ150 ያህል ሰዎች በአብዛኛው ተማሪዎች ሞት ምክንያት የሆነውን የሚያዝያ 2007 ዓ.ም ጥቃት ፈጽሟል፡፡

በሚያዝያ 02 ቀን 2007 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ካራቴን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የካራቴ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከካራቴ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ሸባብ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content