የኩርድ የሠራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ)

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | አውሮፓ እና ዩራሺያ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

የኩርድ የሠራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ) በዋናነት በሰሜን ኢራቅ እና በደቡብ ምሥራቅ ቱርክ የሚንቀሳቀስ ገንጣይ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን በዋናነት በቱርክ ኩርዶች የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1976 ዓ.ም. ኃይል መጠቀም ጀመረ፡፡ የፒኬኬ ዋናው ግብ በደቡብ ምሥራቅ ቱርክ ራሱን የቻለ የኩርድ መንግሥት መመስረት ነው፡፡ በ1980ዎቹ መጀመሪያ፣ ፒኬኬ በገጠር ላይ ከተመሠረተ እንቅስቃሴ ወጥቶ ወደ ከተማ ሽብር ገብቷል፡፡

ፒኬኬ አክራሪ ወታደራዊ ክንፉ ድርጅቱን ሲቆጣጠር እና በራሱ ላይ ጥሎ የነበረውን ተኩስ አቁም ሲሰርዝ ከ1991 ዓ.ም. እስከ 1996 ዓ.ም. የኃይል ድርጊቶች እንደሚፈጽም ገለጸ፡፡ በ2001 ዓ.ም. የቱርክ መንግሥት እና ፒኬኬ የሰላም ድርድራቸውን ቀጠሉ፡፡ ነገር ግን ፒኬኬ በሐምሌ 2003 ዓ.ም. የ13 የቱርክ ወታደሮችን ሕይወት የቀጠፈ ጥቃት ሲፈጽም ድርድሩ ከሸፈ፡፡ ከ2003 ዓ.ም. እስከ 2004 ዓ.ም. ፒኬኬ እና የቱርክ ሠራዊት በተደጋጋሚ ተጋጭተዋል፤ ከእነርሱም መካከል በጥቅምት 2003 ዓ.ም. የተፈጸመው እና ለ24 የቱርክ ወታደሮች ሞት ምክንያት የሆነው ጥቃት ይካተታል፤ ይህ ደግሞ ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ነው፡፡ በ2010 ዓ.ም. ፒኬኬ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በቱርክ የጸጥታ ኃይሎች ላይ ፈጽሟል፤ ከጥቃቶቹ መካከል በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደሮችን የገደለው በቱርክ የጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመ ጥቃት ይገኝበታል፡፡

በመስከረም 28 ቀን 1990 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፒኬኬን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በኋላም በጥቅምት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፒኬኬን ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የፒኬኬ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከፒኬኬ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ፒኬኬ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content