ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በባግዳድ በታኅሳስ 03 ቀን 2012 ዓ.ም. ለዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ኢህሳን አሾዉር አፈና ኃላፊነት ስለሚወስዱት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
አሻዉር የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢራቅ ዜጋ ሲሆን፣ በኢራቅ የነበረው በግል ጉዳዩ ነበር፡፡ በሳዳር ከተማ አቅራቢያ በዋና ከተማው በሚገኘው ታህሪር አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በመካሄድ ላይ ሳለ በአልሸባብ ዲስትሪክት ውሰጥ በግምት 10 የሚሆኑ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች አሻዉርን አፍነው ወስደውታል፡፡ አጋቾቹም ወደ ኢራን ድንበር በመኪና ከማሻገራቸው በፊት አንቀውት፣ ደብድበውት እና በኤሌከትሪክ ጠብሰውት ነበር፡፡ ኢራን ውስጥ ገባ በኋላ የያዙት ሰዎች በስለላ ተሰማርተሃል በሚል ምርመራ አድርገውበታል፡፡ ነገር ግን ሰላይ እንዳልሆነ ከተደረሰበት በኋላ ያዦቹ አሻዉርን ወደ ኢራቅ መልሰውታል፤ በዚያም ሳለ ስቃዩ እና ምርመራው ቀጠለ፡፡ በግንቦት 2012 ዓ.ም. ከእስር ተለቅቆ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልሷል፡፡
