ኸሊል ዩሱፍ ሃርብ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ኸሊል ዩሱፍ ሃርብ፣ በሌላ ስሙ ሳይድ አሕመድ እና አቡ ሙስጣፋ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሃርብ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ተብሎ የተሰየመው ድርጅት ሂዝባላህ መሪ ሃሰን ናስረላህ የቅርብ አማካሪ እና ለአራን እና ፍልስጤም ሽብርተኛ ደርጅቶች ዋነኛ ወታደራዊ አገናኝ በመሆን ሰርቷል፡፡ ሃርብ የሂዝባላህን ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች በፍልስጤም ግዛቶች እና በመላው መካከለኛው ምሥራቅ በበርካታ አገራት አዟል እንዲሁም ተቆጣጥሯል፡፡ ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ ሃርብ በየመን ለሂዝቦላ የፖለቲካ ሸሪኮች ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ በማንቀሳቀስ ላይ ተሳትፏል፡፡

በነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ሃርብ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሃርብ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሃርብ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content