ጀማህ ኢስላሚያ (ጄአይ)

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ጀማህ ኢስላሚያ (ጄአይ) በደቡብ እስያ ላይ የተመሠረተ፣ በቀጠናው እስላማዊ መንግሥት ለመመስረት የሚፈልግ ሽብርተኛ ድርጅት ነው፡፡ ጀማህ ኢስላሚያ (ጄአይ) በጥቅምት 1994 ዓ.ም. በባሊ ጭፈራ ቤት ተፈጽሞ ከ200 በላይ ሰዎችን የገደለውን ጥቃት፣ 12 ሰዎችን የገደለው በጃካርታ ማሪዮት ሆቴል የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት እና በጥቅምት 1998 ዓ.ም. በባሊ የተፈጸመው ለ26 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት የመሳሰሉ ከፍተኛ የሽብርተኛ ጥቃቶች ፈጽሟል፡፡

በጥቅምት 13 ቀን 1995 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጀማህ ኢስላሚያ (ጄአይ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የጀማህ ኢስላሚያ (ጄአይ) ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከጀማህ ኢስላሚያ (ጄአይ) ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡

Skip to content