ስለ ተቋሙ
ሮታ ለፍትሕ ስለ ጃበር ኤ. ኤልባነህ፣ በሌላ ስሙ ጃበን ኤ. ኤልባነልት እና አቡ ጁባር መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኤልባነህ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተሰየመው አል-ቃዒዳ የማቴሪያል ድጋፍ በማድረግ ወይም እንዲህ ያለውን ድጋፍ ለማድረግ በመመሳጠር ምክንያት ክስ ተመስርቶበታል፡፡ ኤልባነህ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው በየመን ነበር፡፡ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተካቷል፡፡
