ኢብራሂም አል-ባና

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወታደራዊ እና የደህንነት አመራር ይሰጥ ነበር፤ አል-ባና ከአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) መሥራች አባላት መካከል አንዱ ነው፡፡

በአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) ኢንስፓየር የተባለ የእንግሊዝኛ መጽሔት የ2002 ዓ.ም. እትም፣ አል-ባና በመስከረም 01 ቀን 1994 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ሞራላዊ መሆኑን በመግልጽ፣ አሜሪካ በውጭ አገራት ለምትወስዳቸው እርምጃዎች በዓለም ዙሪያ አሜሪካዊያንን ዒላማ በማድረግ ምላሽ እንደሚሰጥ አስጠንቅቋል፡፡ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ አባል ከመሆኑ በፊት፣ አል-ባና ከ1988 ዓ.ም. እስከ 1990 ዓ.ም. በየመን የግብጽ የኢስላሚክ ጅሃድ መሪ ሆኖ ሰርቷል፤ በመቀጠልም የቡድኑ የሥልጠና እና ስለላ ዘርፎች ኃላፊ ሆኖ ሰርቷል፡፡

በግንቦት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ባና ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ባና ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ባና ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ለዚህ ቡድን ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content