ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ኢብራሂም አሕመድ ማህሙድ አል-ቃሲ፣ በሌላ ስሙ ሼክ ኹባይብ አል-ሱዳኒ እና መሐመድ ሳላህ አህመድ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $4 ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ቆሲ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተሰየመው በአረቡ ባሕረሰላጤ (ኤኪውኤፒ) የአል-ቃዒዳ ከፍተኛ መሪ ነው፡፡
አል-ቃሲ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳን የተቀላቀለው በ2006 ዓ.ም. ነበር፤ ለረጅም ጊዜ በንቃት ሲንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን፣ ለበርካታ ዓመታትም ለሟቹ የአል-ቃዒዳ መሪ ኡሳማ ቢን ላዲን ሰርቷል፡፡ አል-ቆሲ ወደ ጓንታናሞ ቤይ ከመዘዋወሩ በፊት በታኅሳስ 1994 ዓ.ም. በፓኪስታን ተያዘ፡፡ በ2002 በወታደራዊ ኮሚሽን ፊት ከአል-ቃዒዳ ጋር መመሳጠሩን በመግለጽ ጥፋተኛ መሆኑን አምኗል፡፡ በቅድመ ፍርድ ስምምነትም መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ አል-ቃሲን ከእስር በመልቀቅ ወደ ሱዳን መልሳለች፡፡
ከ2007 ዓ.ም. ጀምሮ አል-ቆሲበ በአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የምልመላ ማቴሪያሎች ላይ ታይቷል፤ በኦንላይን ፕሮፖጋንዳ አማካኝነትንም ሎን-ዎልፍ ዓይነት ጥቃቶች በዩናይትድ ስቴትስ ላይ እንዲፈጸሙ ሲያበረታታ ቆይቷል፡፡ በአንድ ወቅትም የሟች የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ኢምር ቃሲም አል-ሪሚ እገዛ ይሰጥ የነበረ ቡድን አባል በመሆን አገልግሏል፡፡
