ሃራካት አል-ሙቃዋማ አል-ኢስላሚያ (ሃማስ)

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ሃራካት አል-ዋቃዋማ አል-ኢስላሚያ (ሐማስ) በመጀመሪያው የፍልስጤም አመጽ ወይም ዘ ፈርስት ኢንቲፋዳ ሲጀመር ሙስሊም ወንድማማቾች የፍልስጤም ቅርንጫፍ አካል ሆኖ ተመሰረተ፡፡ ሃማስ፣ ኢዝ አል-ዲን አል-ቃሲም ብርጌድ ተብሎ የሚጠራ ወታደራዊ ክንፍ አለው፤ ይህ ክንፍ ከ1980ዎቹ ጀምሮ የእስራኤል እና የፍልስጤም ግዛቶች ላይ ጥቃቶች ፈጽሟል፡፡ እነዚህ ጥቃቶች በእስራኤል የሲቪል ዒላማዎች ላይ ሰፋፊ መጠን ያላቸው የቦምብ ፍንዳታዎች፣ በትንንሽ መሣሪያዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች እና የተደበቁ በመንገድ ዳር የሚቀመጡ ፈንጂዎች እና የሮኬት ጥቃቶች ተፈጽሟል፡፡ ሐማስ በነሐሴ 1993 ዓ.ም. ለተፈጸመው እና ሁለት አሜሪካዊያንን ጨምሮ 15 ሰዎችን ለገደለው እና ከ120 በላይ የሆኑትን ደግሞ ላቆሰለው የኢየሩሳሌም ስባሮ ፒዜሪያ ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡ በሚያዝያ 2008 ዓ.ም. አንድ የሃማስ አባል ለ20 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነ ጥቃት በአውቶብስ ላይ ፈጽሟል፡፡

በመስከረም 28 ቀን 1990 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃማስን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በኋላም በጥቅምት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃማስ ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሃማስ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሃማስ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሃማስ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content