ፋከር ቤን አብደልአዚዝ ቦውሶራ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ | ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ፋከር ቤን አብደልአዚዝ ቦውሶራ በሌላ ስሙ አቡዩሲፍ አል-ቱኒዚ ወይም ፋከሩን መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ቦውሶራ በአል-ቃዒዳ (ኤኬው) እየሰለጠነ እና አጥፍቶ ጠፊ የመሆን ሀሳብ እንዳለው የሚያስታውቅ ነው፡፡ ከኢስላማዊ አክራሪዎች ጋር ከፍተኛ ግንኙነት ያለው ይህ ግለሰብ የቱኒዝያዊው የአል-ቃዒዳ የሽብር ተጠርጣሪ አብደራዉፍ ጅደይ (ሀይፐርሊንክ) ጋር ግንኙነት አለው፡፡ ቦውሶራ በ1980 ዓ.ም. ከትውልድ አገሩ ቱኒዝያ ወጥቶ ፈረንሳይ ገባ፡፡ በ1983 ዓ.ም. ደግሞ ከፈረንሳይ ወጥቶ ወደ ሞንትሪያል፣ ካናዳ ተዘዋወረ፤ ከዚያም በ1980ዎቹ አመታት በካናዳ እና በቱኒዝያ መካከል ይመላለስ ነበር፡፡ ቦውሶራ በ1991 ዓ.ም. የካናዳ ዜግነት አገኘ፡፡ በዚያው አመት ቦውሶራ ከካናዳ ወደ አፍጋኒስታን ሄዶ ከአልቃይዳ የሽብርተኝነት ስልጠና አግኝቷል፡፡ ቦውሶራ በመቀጠል ወደ ካናዳ ተመለሰ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የት እንደሚገኝ አይታወቅም፡፡ ቦውሶራ ወደ ካናዳ ወይም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሊመለስ እና የሽብር ጥቃቶች ሊያቅድ ሊፈፅም ይችላል ብለው ባለስልጣናት ይሰጋሉ፡፡ ይህ ግለሰብ ከፍተኛ ህመም ያለበት እና ጤናውም በጣም የታወከ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሰውነት መቀነስ እና የአካላዊ ሁኔታውም የተቀየረ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡

Skip to content