ስለ ተቋሙ
የግብጽ ኢስላማዊ ጂሃድ (ኢአይጄ)፣ በሌላ ስሙ አል-ጂሃድ በ1960ዎቹ የተመሠረተ የግብጽ አክራሪ ድርጅት ነበር፡፡ የግብጽ ኢስላማዊ ጅሃድ ዋነኛ ግብ የግብጽን መንግሥት መጣል እና በኢስላማዊ መንግሥት መተካት ነበር፡፡ ይህ ቡድን በዋናነት የግብጽ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ በጦር መሣሪያ ጥቃት ያደርስ ነበር፡፡ በአይመን አል-ዛዋሂሪ ይመራ የነበረው ጂአይጄ በሰኔ 1993 ዓ.ም. ከአል-ቃዒዳ ጋር ተዋሃደ፡፡
