ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በ1995 ዓ.ም. በቤይት ሀኖውን በጋዛ ሰርጥ በዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ ስለተፈፀመው የቦምብ ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በጥቅምት 04 ቀን 1996 ዓ.ም. አራት የዩናይትድ ስቴትስ የፀጥታ አባላት ይዞ ይጓዘ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በተደበቀ ፈንጂ አማካይነት ጥቃት በመድረሱ ሶስቱን ሰዎች ሲገድል አራተኛው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ እነዚህ የጥቃቱ ሰለባዎች ለዩናይትድ ስቴትስ የመካከለኛው ምስራቅ ልዑክ አባላት ጥበቃ በማድረግ ላይ ነበሩ፡፡ ልዑካኑ ደግሞ ለፉልብራይት ስኮላርሽፕ ላመለከተ የፍልስጤማዊ ተማሪ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ወደ ጋዛ በመጓዝ ላይ ነበሩ፡፡
