አል-ቃዒዳ በዓረብ ባሕረሰላጤ (አኪውኤፒ)

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የየመን እና የሳውዲ የሽብር ኃይሎች ከተዋሃዱ በኋላ በጥር 2001 የተመሠረተ ነው፡፡

የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ካስመጣቸው ግቦች መካከል፡- በአረብ ባሕረ ሰላጤ እና በሰፊው መካከለኛው ምሥራቅ እስላማዊ መንግሥት ወይም ካሊፌት መመስረት እና የሸሪዓ ሕግን ተግባራዊ ማድረግ አንዱ ነው፡፡ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ በአረብ ባሕረ ሰላጤ ውስጥ አካባቢያዊ፣ የዩናይትድ ስቴትስን እና የምዕራቡን ዓለም ጥቅሞች ዒላማ አድርጓል፡፡ ይህ ቡድን ለበርካታ የሽብር ጥቃቶች ኃላፊነት የወሰደ ሲሆን ከእነርሱም መካከል በጥር 2007 ዓ.ም. በፓሪስ ውስጥ በቻርሊ ሄብዶ የጋዜጣ አሳታሚ መሥሪያ ቤት ላይ የተፈጸመውን እና የ12 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው ጥቃት ይገኝበታል፡፡

የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ የአል-ቃዒዳ ተባባሪ የሽብር ድርጅት ነው፤ ከአል-ቃዒዳ ዓለም ዓቀፍ አመራር ጋር በመስራት የምዕራቡን ዓለም ዒላማ አድርጎ ይሰራል፤ ከሌሎች ተባባሪ ድርጅቶችም ጋር ያለውን ትብብር ያጠናክራል፡፡ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ቁልፍ እሴት ከአል-ቃዒዳ ሰፊ ኔትወርክ ጋር ያለው የፋይናንስ እ የማሳለጥ ግንኙነት ነው፡፡

የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ በታኅሳስ 16 ቀን 2002 ዓ.ም. ኡመር ፋሩቅ አብዱልሙጠሊብ የተባለ አሸባሪ በሰውነቱ ላይ በታሰረ ቦምብ አንድን አውሮፕላን ለማውደም ቢሞክርም ሙከራው አልተሳካም፡፡ እንዲሁም ይህ ቡድን በ2002 ዓ.ም. መጨረሻ በሁለት የጭነት አውሮፕላኖች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመጓጓዝ በነበሩ ፕሪንተሮች ውስጥ ፈንጂዎች ደብቆ ነበር፤ አውሮፕላኖቹ በሁለት ስፍራዎች ሲያርፉም ቦምቦቹ በጥቅምት 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ተገኝተው ጉዳት አላደረሱም፡፡

በጥር 11 ቀን 2002 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት እንዲሁም ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው ሰይሞታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከየአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም ለኤኪውአይኤስ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content