አል-ሞርቢቶዉን

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

አል-ሙራቢቶዉን፣ ቀደም ብሎ የአል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ (ኤኪውአይኤም) አካል የነበረ ሲሆን፣ በኋላ መሪው ሞኽታር በልሞኽታር በምዕራቡ ዓለም ጥቅሞች ላይ ጦርነት ለመክፈት በመዛት አል-ሙላታሙን ሻለቃ መቋቋሙን አሳወቀ፡፡ በ2005 ዓ.ም. ሙላታሙን ሻለቃ እና በማሊ የሚገኘው ሙቭመንት ፎር ዩኒቲ ኤንድ ጂሃድ ኢን ዌስት አፍሪካ (ኤምዩጄኤኦ) ተዋህደው “አል-ሙራቢቶዉን” በሚል ስም እንደሚጠሩ አሳወቀ፡፡ በ2007 ዓ.ም. አል-ሙራቢቶዉን ከኤኪአይኤም ጋር መዋሃዱን ሲገልጽ፣ አል-ሙራቢቶዉን በ2009 ዓ.ም. ከሌሎች ሦስት ክልላዊ ሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር በመዋሃድ ጃማዓት ናስር አል-ኢስላም ዋል ሙስሊሚን (ጄኤንአይኤም) መሠረተ፡፡

በጥር 2005 ዓ.ም. አሁን ልአል-ሙራቢቶዉን በመባል የሚጠራው ድርጅት በአደቡብ ምሥራቅ አልጄሪያ በአሜናስ አካባቢ በሚገኝ ቲጉኤንቶሬይን የነዳጅ ተቋም ላይ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡ በአራት ቀናቱ ከበባ 800 የሚያህሉ ሰዎች ታግተው ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ጨምሮ ሰላሳ ዘጠኝ ንጹሃን በዚህ ጥቃት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በኅዳር 2007 ዓ.ም. አል-ሙራቢቶዉን በባማኮ በሚገኝ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ላይ ጥቃት ፈጽመው የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ጨምሮ 170 ሰዎችን አገቱ፡፡ በዚህ ጥቃት ከሞላ ጎደል 27 ሰዎች ሞተዋል፤ ከእነርሱም መካከል አንድ የአሜሪካ የዓለም ዓቀፍ ልማት ሠራተኛ ይገኝበታል፡፡ አል-ሙራቢቶዉን በቡርኪናፋሶ በተፈጸገመው እና የአሜሪካ ዜጋን ጨምሮ ለ30 ያህል ሰዎች ሞት ምክንያት በሆነ በታዋቂ የቱሪስት ሆቴል ላይ በኤኪውአይኤም በጥር 2008 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ተሳትፎ ነበረው ተብሏል፡፡

በታኅሳስ 10 ቀን 2006 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጀመሪያ ሙላታሙን ሻለቃ ተብሎ ይጠራ የነበረውን አል-ሙራቢቶዉን በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በማለት በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት ሰይሞታል፡፡ ቀደም ብሎ በታኅሳስ 9 ቀን 2006 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ሙራቢቶዉን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ አል-ሙራቢቶዉን አሁንም ቡድኑ ዋነኛ ስም ሆኖ የገለግላል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ሙራቢቶዉ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ሙራቢቶዉ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ሙራቢቶዉን/አል-ሙላታሙን ሻለቃ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content