ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አሃዶን አዳክ ተብሎ ስለሚታወቀው የሞሮ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኤምኤንኤንኤፍ) ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $ 250,000.00 ወሮታ ይከፍላል፡፡
በመስከረም 19 ቀን 2002 ዓ.ም. በጆሎ ደሴት፣ ፊሊፒንስ ኤምኤንኤልኤፍ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ጭነት ስር ፈንጂ በማስቀመጥ አፈንድቷል፡፡ ይህ ፍንዳታ ሁለት የአሜረካ ወታደሮችን እና የፊሊፒንስ መከላከያ ሰራዊት ወታደር ገድሏል፡፡ ሟቾች ትምህርት ቤት ለመገንባት ይሰራ የነበረ ሰብአዊ ሚሲዮን አካል ነበሩ፡፡ በግንቦት 13 ቀን 2002 ዓ.ም. የፊሊፒንስ 9ኛ ችሎት አዳክ ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር እንዲውል የእስር ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
