[email protected]

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ የሂዝባላህ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አድሀም ሁሳያን ታባጃ ወይም በሌላ ስሙ አድሃም ታባጃ የሂዝባላህ አባል ሲሆን ከከፍተኛ የሂዝባላህ ድርጅታዊ አካላት ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ሲሆን ግንኙነቱም ኢዝላሚክ ጅሃድ የሚባለውን የቡድኑ የኦፕሬሽን አካልን ይጨምራል፡፡

ታባጃ ሂዝባላህን በመወከል በሊባኖስ ውስጥ ንብረቶች አሉት፡፡ ይህ ግለሰብ በሰኔ 2007 በዩናይትድ ስቴትስ የየገንዘብ ሚኒስቴር ማዕቀብ የተጣለበት አል-ኢንማ ግሩፕ ፎር ቱሪዝም ወርክስ የተባለ የሪል እስቴት ልማት እና የግንባታ ድርጅት ዋነኛ የአክሲዮን ባለድርሻ ነው፡፡ የታባጃ ኩባንያ አል-ኢልማ ኢንጅነሪንግ እና ኮንትራክቲንግ ኩባንያ ከ1980ዎቹ መገባደጃ ጀምሮ በሊባኖስ ውስጥ ታላቅ እና እጅግ ስኬታማ ከሆኑ የሪል እስቴት ድርጅቶች መካከል አንዱ ነው፤ ይህ ድርጅት በሂዝባላህ እንደ ኢንቨስትመንት ዘዴ ያገለግላል፡፡ በ1998 ታባጃ ከሂዝባላህ መሪዎች ጋር የነበረውን ቁርኝት በመጠቀም በሂዝባላህ ቁጥጥር ስር ባለው የቤይሩት ክፍል ዳሂህ እና በደቡብ ሊባኖስ አል-ኢንማ ኢንጅነሪንግ እና ኮንትራክቲንግ ብቸኛ የዚህ ዘርፍ ኩባንያ እንዲሆን እና በሞኖፖሊ እንዲይዝ ተጠቅሞበታል፡፡ በቅርቡ ታባጃ የአል-ኢንማ ኢንጅነሪንግ እና ኮንትራክቲንግ ኩባንያ የኢራቅ ቅርንጫፎችን በመጠቀም ለሂዝባላህ የገንዘብ ድጋፍ እና ድርጅታዊ መዋቅር ለመስጠት የሚያስችል የነዳጅ ዘይት እና የግንባታ ልማት ፕሮጀክቶችን ተጠቅሟል፡፡ ታባጃ እና የእርሱ ኩባንያዎች በባግዳድ፣ ኢራቅ የግሪን ዞን ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ ስራዎች ለማግኘት ጥሯል፡፡ ታባጃ ከሂዝባላህ የፓለቲካ ሀላፊ ሙሀመድ ታውታሪኒ እና ከሌሎች ሀላፊዎች ጋር በእነዚህ ፕሮጀክቶች ጉዳይ ሰርቷል፡፡

በሰኔ 03 ቀን 2007 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የየገንዘብ ሚኒስቴር ታባጃን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የታባጃን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከታባጃ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ በተጨማሪም፣ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ የሽብር ድርጅት ተብሎ ለተሰየመው ለሂዝባላህ ሆነ ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ ወይም ለማቅረብ መሞከር ወይም መመሳጠር የወንጀል ድርጊት ነው፡፡ ሳውዲ-አረቢያም እንዲሁ ታባጃን እና የእርሱን ኩባንያዎች ሽብርተኞች በማለት መዝግባለች፡፡

Skip to content